Non ti piace? Non importa! Puoi restituire gli articoli fino a 30 giorni
Non puoi sbagliarti con un buono regalo. Con il buono regalo, il destinatario può scegliere qualsiasi prodotto della nostra offerta.
Fino a 30 giorni per il reso
አገራችን ኢትዮጵያ በመንፈሳዊ፣ በፍልስፍናዊ፣ በሥነ-መንግሥታዊ እና በማኅበረሰባዊ ዘርፎች ልዩ ስፍራ እንድትይዝ ያደረጓት አዎንታዊ እሴቶችና አስተሳሰቦች ለመኖራቸው ግልጽ ማስረጃው በዓለም ታሪክ ውስጥ በሺህዎች ዓመታት የሚቆጠር የሥነ መንግሥትና የአገር ታሪክ ያላት መሆኗ ነው። ይህ ልዩ ማንነት መሠረቱ የሕዝቧ ሃይማኖት፣ ባህል እና በረጅም ዘመናት ውስጥ በተፈጠረ ታሪካዊ ሒደት እና መስተጋብር የተቀረጸው ኢትዮጵያዊነት የተሰኘ የጋራ ማንነት ነው። ይህ ማንነት የጭቆና ሰለባ የሆኑ ሌሎች ሕዝቦችም ለነጻነታቸውና ለሰብዓዊ ክብራቸው እንዲቆሙ የሚያነሣሣ ተምሳሌት በመሆኑ የሰው ልጆችን አንድነትና እኩልነት የማይቀበሉ ዘረኛ ኃይሎችና ቅኝ ገዥዎች በተለያዩ ዘመናትና በብዙ መንገዶች ይህንን ልዩ ማንነት ለማዳከምና ለማጥፋት ሲሞክሩ ቆይተዋል። ሆኖም ግን በሕዝቡ ጽናት፣ በባህሉ ጥልቀት እና በእምነቱ ጥንካሬ የተደገፈው ኢትዮጵያዊነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሻግሮ በመቀጠል የአገሪቱ ዋና መለያና የአንድነቷ መሠረት ሆኖ ዘልቋል።
የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ለጥፋት ዓላማቸው ሲሉ ሐሰተኛ ትርክቶችን በመፍጠርና በማስፋፋት ኢትዮጵያዊነትን ከንዑስ የጎሣ ወይም የብሔር ማንነት በታች አውርደው የሚመለከቱ አስተሳሰቦችንና ተከታዮቻቸውን ለመፍጠር ችለዋል። ይህም በኢትዮጵያውያን መካከል ጥላቻን፣ መከፋፈልንና አለመተማመንን በማባባስ የማኅበራዊ አንድነት መሠረት እንዲሸረሸር አድርጓል። የዚህ መጽሐፍ ዋና ትኩረት ኢትዮጵያዊነትን፣ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና ከእርሷ ጋር የተሳሰሩትን ነባር ማኅበረሰባዊ፣ ሥነ-መንግሥታዊና ባህላዊ እሴቶችን ለማዳከም ወይም ለማጥፋት ከተንቀሳቀሱ ኃይሎች መካከል አንዱ ተደርጎ የሚታየውን እና የተረፈ ናዚ አስተሳሰብ የሆነውን ኦነጋዊ ኦሮሙማ ታሪካዊ ሚናና በዘመናችን ያለውን ተጽዕኖ መመርመር ነው።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የጥንት ጀርመናውያን ሃይማኖትና ባህል ተብለው የሚገለጹት አስተምህሮዎች፣ ሥርዓተ አምልኮዎች፣ መዝሙራት፣ የመሥዋዕት አቀራረቦች እንዲሁም ስለ አማልክቶቻቸውና መናፍስቶቻቸው የነበራቸው እምነቶች በሰፊው ተብራርተው ቀርበዋል። በተመሳሳይም በዘመናችን የኦሮሞ ባህላዊ እምነት የሆነው ዋቄፈታ ከኦነጋዊ ኦሮሙማ አስተሳሰብ ጋር ተዋሕዶ ወደ ዘር ተኮር የፖለቲካ ንቅናቄ እና ተቋማዊ አደረጃጀት የተሸጋገረበትን ሂደት ይመረምራል። በተለይም ከናዚዝም በኋላ የተፈጠሩ አንዳንድ የጀርመን ድርጅቶችና አስተሳሰቦች በብዙ ዓመታት ውስጥ በዚህ ሂደት ላይ እንዴት ተሳትፈው እንደሠሩ እና በራሳቸው አምሳል እንዴት ቅርጽ ለመስጠት እንደሞከሩ በዝርዝር ያብራራል።
ይህ መጽሐፍ ይህንን ታሪካዊ ሂደት እና ትስስር በጥልቀት በመረዳት የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ሌሎች
Ciao! Sono Libroamiko, il tuo consulente di libri.
Come posso aiutarti?